ዶ/ር ሙሉ ነጋ ካሕሳይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ ተግባራዊ የሚሆን ደንብ አጽድቋል።

ይህንን ተከትሎ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ካሕሳይ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ የሾመ ሲሆን ዋና ሥራ አስፈጻሚው የክልሉን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትን የሚመሩ ኃላፊዎችን፣ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመመልመል እንደሚሾሙ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፌስቡክ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።