EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዘንድሮ ከውጭ ጎብኚዎች ከ5.2 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዘንድሮ ከዓለም አቀፍ የኮንፈረንስ ቱሪዝምና ከውጭ ጎብኚዎች ከአምስት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት “አዲሱ የኢኮኖሚ ሞተር” በሚል ርዕስ የቱሪዝም ዘርፉን በተመለከተ ከኤን ቢ ሲ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ አመት ከአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን በላይ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ኢትዮጵያን የጎበኙ መሆናቸውን ጠቅሰው ይህም ከአምናው ጋር ሲነጻጸር የ100 ሺህ ጎብኚዎች ብልጫ አሳይቷል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘንድሮ ከ50 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥ ተንቀሳቅሰው የተለያዩ መዳረሻዎችን መጎብኘታቸውን ገልጸው ከሀገር ውስጥ ቱሪዝም 79 ቢሊየን ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ባስተናገደቻቸው 204 ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች 166 ሺህ ሰዎች መሳተፋቸውን ገልፀዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews