ጠ/ሚ አቢይ በሶማሌ ክልል ቀብሪበያን ዛሬ ማለዳ ጎብኝተዋል።
ጠ/ሚ አቢይ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን ዛሬ ማለዳ ጎብኝተዋል። በጊዜያዊነት የውኃ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችን፣ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ እና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን አቅርቦት እናሳድጋለን እና ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የጀመርናቸውን የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልን።
Telegram: https://t.me/ebstvworldwide
Follow us on: https://linktr.ee/ebstelevision#ኢቢኤስ#EBS