LatestNewsPolitics

ቦርዱ ሕጋዊ ምዝገባ ላጠናቀቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ምልክት እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ለማከናወን ሕጋዊ ምዝገባ ላጠናቀቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከጥር 13 እስከ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም ባሉት ቀናት የምርጫ ምልክት እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርቧል።የምርጫ ምልክት መረጣው በሚከተለው መልኩ እንደሚከናወንም አመላክቷል፤1. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ ምልክትነት ሊሆኑ የሚችሉ የተለያዩ ምልክቶችን ያዘጋጀ ሲሆን የፓርቲ ተወካዮች ከተዘጋጁት ምልክቶች ሊወክለኝ ይችላል የሚሉትን ይመርጣሉ።2. የመረጡት ምልክት በፓርቲያቸው የተያዘ መሆኑን ያስመዘግባሉ፤ አንድ ፓርቲ ያስመዘገበው ምልክት ከሚመረጡ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ ይወጣል።3. በቦርዱ ከተዘጋጀው ምልክት ውስጥ የሚፈልጉትን ምልክት ያላገኙ/ወይም የራሳቸውን ምልክት ማስመዝገብ የሚፈልጉ ፓርቲዎች የሚከተሉትን ነገሮች ማሟላት አለባቸው።– ምልክታቸውን አትመው ለማስመዝገብ ይዘው መምጣት አለባቸው።– የምልክታቸውን ዲጂታል ፎርማት በፍላሽ ማቅረብ አለባቸው።– ምልክታቸው በጥቁር እና ነጭ ቀለም የተዘጋጀ መሆን አለበት።– ምልክታቸው 2 ሲሜ በ2 ሴንቲ ሜትር መሆን አለበት– የጥራት መጠኑ 200 እስከ 300 ፒክስል መሆን አለበት– የፋይሉ መጠን ቢበዛ 200 ኪሎ ባይት መብለጥ የለበትም4. የምርጫ ምልክት መረጣው የሚከናወነው ከጥር 13 ቀን እስከ ጥር 18 ሲሆን ቦርዱ ከጥር 18 እስከ ጥር 24 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ የማጣራት እና የመወሰን ተግባራትን ያከናውናል ተብሏል።5. ከጥር 13 እስከ ጥር 18 ቀን 2013 በሚደረገው የምልክት መረጣ ላይ ማንኛውም ሕጋዊ ምዝገባቸውን ያጠናቀቁ ፓርቲዎች በሥራ ሰዓት ቦሌ ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት ባለው የሺ ሕንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው የፖለቲካ ፓርቲዎች ማዕከል ይከናወናል ብሏል ቦርዱ።6. ይህ የምርጫ ምልክት መረጣ የግል እጩዎችን የማያካትት ሲሆን፣ የግል እጩዎች ምልክታቸው የሚመርጡበት መንገድ ወደፊት በቦርዱ የሚገለጽ መሆኑንም ቦርዱ ገልጿል።