News

አዲስ ነገር – በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን የርዕደ መሬት አደጋ፡፡

🇵🇰#ፓኪስታን
በፓኪስታን እና አፍጋኒስታን በደረሰ የርዕደ መሬት አደጋ በትንሹ 13 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል፡፡
6.5 ሬክተር ስኬል በተመዘገበው በዚሁ ርዕደ መሬት በምዕራብ ፓኪስታን 8 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 44 ክፉኛ መጎዳታቸው ሲነገር በሃገረ አፍጋኒስታን በአደጋው 4 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገው 50 ያክሉ ክፉኛ መቁሰላቸው ነው የተነገረው፡፡
በአገራቱ በደረሰው በዚሁ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በርካታ የመሰረተ ልማቶች እና ህንፃዎች በአደገኛ ሁኔታ መውደማቸውን የዘገበው አልጀዚራ ነው ።
🇷🇺#ሩሲያ
ሩሲያ የጀመረችውን የሚሳኤል የመከላከያ ሥርአት የማዘመን ሥራ በዚህ አመት መጨረሻ ያልቃል አለች።
የሩሲያው የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ የሩሲያ የሚሳኤል መከላከያ ሥርአት የማዘመን ሥራ በአውሮፓውያኑ 2023 መጨረሻ የሚያልቅ መሆኑን ገልጸው “እድሜ ለብርቱው የሚሳኤል ጋሻ ሥርአታችን በምስራቅ ዩክሬን ከኪይቭ የተቃጡብንን የሚሳኤል ጥቃቶች ሁሉንም አክሽፈናል” ብለዋል ።
መከላከያ ሚኒስትሩ የሩሲያ የአየር ሀይልን ለማዘመን የሚያስችሉ 621 ግዙፉ ወታደራዊ መሰረተ ልማቶችን ግንባታ እየተፋጠነ ሲሆን የረቀቁ የአየር ሀይል ቴክኖሎጂዎች 85 ከመቶ ለማድረስ እየተሰራ ነው ማለታቸውን አናዶሉ ዘግቧል ።
🇺🇦#ዩክሬን
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም “አይኤም ኤፍ” ለዩክሬን የ15 .6 ቢሊዮን ዶላር ብድር ድጋፍ አፀደቀ፡፡
የገንዘብ ተቋሙ ለዩክሬን ይፋ ያደረገው የ15.6 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ በጦርነቱ ምክኒያት መንግስት ያጋጠመውን የፋይናንስ እጥረት የሚሞላ እና የአገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ የሚረዳ መሆኑ ነው የተነገረው ።
የዩክሬን የገንዘብ ሚኒስቴር የገንዘብ ተቋሙ ይፋ ያደረገው ድጋፍ ለአገሪቱ የጥቅል ምጣኔ ሃብት መረጋጋት ጉልህ አስተዋፅኦ ያለዉ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ የልማት አጋር አካላት ዩክሬንን እንዲደግፉ ያበረታታል ብሏል በመግለጫው ።
የዩክሬን አገራዊ የጥቅል ምርት በአውሮፓውያኑ 2022 በ30 ከመቶ መቀነሱን የዘገበው ኤፒ ነው።
#የሳህል ቀጠና
በአፍሪካ በሳህል ቀጠና በሽብርተኛች በሚደርስ ጥቃት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በ2ሺ ከመቶ መጨመሩን አንድ ጥናት አመለከተ ።
በሳህል ቀጠና ባለፉት 15 አመታት በአሸባሪዎች በሚቃጡ ጥቃቶች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር በ2ሺ ከመቶ ሲያሻቅብ በሽብርተኝነት ህይወታቸውን ያጡ ዜጐች ቁጥር ከ22 ሺ አልፏል ሲል የአውስትራሊያ ተቋም ገልጧል፡፡
መቀመጫውን አውስትራሊያ ያደረገው ተቋሙ ባወጣው ጥናቱ በዓለም ላይ በሽብር ጥቃት ባለፉት 15 አመታት ከተገደሉት ሰዎች ውስጥ 47 ከመቶ ከሳህል ቀጠና አገራት ናቸው ሲል አስታውቋል።
በመላው ዓለም በሽብር ጥቃት እጅጉን ከተጎዱ አገራት ዝርዝር ውስጥ የመጀመሪያዎቹ 10ሩ ከሳህል ቀጠና መሆናቸውን አናዶሉ ዘግቧል።

ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ

👉 የማለዳ ዜና ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት እስከ 2:00 / በድጋሚ ከ ጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:30 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት (በቀጥታ)

👉 የምሽት ዜና ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00

ዘወትር ቅዳሜ

👉 የእኩለ ቀን ዜና ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ ዜናዎች በፍጥነት እና በየእለቱ ይዘገቡበታል።

አዲስ ነገር / What’s New