News

ኢሰመኮ በኢትዮጵያ ያለው የጋዜጠኞች እስር እንደሚያሳስበው ገለጸ::

የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ በኢትዮጵያ ያለው የጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች እስር እንደሚያሳስባቸው ገለጹ፡፡
ኮሚሽነሩ ዛሬ የሚከበረውን የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን አስመለክተው በሰጡት ማብራሪያ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ መከታተል አንዱ የፕሬስ ነጻነት አካል ነው በማለት አጠቃላይ የተቋማቱ ስራ በተለያዩ ተግዳሮቶች እየተፈተነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አክለውም ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ባሳለፍነው እሁድ እለት እንደታሰረና አሁን የት እንዳለ እንደማይታወቅም ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ዳንኤል በመግለጫቸው የመገናኛ ብዙሀን ካለባቸው ተግዳሮቶች መካከል ግብር፣ የመረጃ እጥረት፣ የመሰረተ ልማት ችግሮች እንደሚገኙባቸው ገልጸው ችግሮቹ የሚመለከተው አካል ሁሉ በትብብር መስራት እንዳለበት የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል፡፡