EthiopiaNews

የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግንባታ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቢሾፍቱ እያስገነባው ለሚገኘው አየር ማረፊያ በአሁኑ ወቅት ለመሬት መደልደል፣ ለአጥር እና የውሃ መሰረተ ልማቶች ጨምሮ ለቅድመ ግንባታ ስራዎች ከ750 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጉን ገልጿል።

አየር መንገዱ ይህን የገለጸው 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማስመልከት የደንበኞች ተሞክሮ ቀን መርሃ ግብርን በትላንትናው ዕለት ባከናወነበት ወቅት ነው።

በመድረኩ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገው 12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ለመሸፈን አሜሪካን ጨምሮ ከቻይና፣ አውሮፓ፣ እስያና መካከለኛው ምስራቅ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸውን አብራርተዋል።

ሚንስትሩ አያይዘውም ከጠቅላላው ወጪ ውስጥ 8 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው ከውጭ ብድር የሚገኝ ነው ያሉ ሲሆን ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የካፒታል መዋጮ የሚሸፈን መሆኑንም አንስተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በፕሮጀክቱ ምክንያት ከቀያቸው የተነሱ አርሶ አደሮች የመኖሪያ መንደር ተገንብቶላቸው የገቢ ማስገኛ ስራዎችም የተመቻቹላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv