InternationalNews

የቻይናው መሪ በሰሜን ኮሪያ

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ግብዣ በቀጣይ ሳምንት ሰሜን ኮሪያን እንደሚጎበኙ ተነገረ።

ሺ ጂንፒንግ በቀጣይ ሳምንት ሰኔ 1 እና 2 በሰሜን ኮሪያ የሁለት ቀናት ጉብኝት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ ከፈረንጆቹ 2019 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ፒዮንጊያንግ እንደሚያመሩም ነው የተገለጸው፡፡

የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግኡን በበኩላቸው ቻይና በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጃፓንን የረታችበትን 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ለመገኘት ከወራት በፊት ቤጂንግ መጎብኘታቸው ተጠቅሷል፡፡

የቻይናው ፕሬዝዳንት ወደ ሰሜን ኮሪያ የሚያቀኑት ደግሞ በሰሜን ኮሪያ ላይ ሁለት ተቃራኒ ግንኙነት ያላቸውን የሩሲያና የአሜሪካን መሪዎች ተቀብለው ካነጋገሩ ከሳምንታት በኋላ መሆኑም ነው የተመለከተው፡፡ አር ቲ እንደዘገበው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv