InternationalNews

በቻይና ድራማዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ ዘመቻ

ቻይና በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚንሸራሸሩ ከባህል ያፈነገጡ ድራማዎች ላይ እርምጃ መውሰድ የሚያስችል ዘመቻ መጀመሯ ተሰምቷል።

የቻይና መንግስት አደና የወጣባቸው እነዚህ ድራማዎች ልቅ ወሲብን የሚያበረታቱ፣ ግጭትን የሚቀሰቅሱና ቁሳዊ ማንነትን መገንባት ላይ የሚያጠነጥኑ ይዘት ያላቸው አጫጭር ድራማዎች ናቸው ተብሏል፡፡

እነዚህ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ድራማዎች ሰዎች ስለትዳርና የፍቅር ግንኙነት የተሳሳተ መረጃ እንዲኖራቸው ከማድረግ ባለፈ ሰዎች በአቋረጭ ሀብት ማካበትና ቁሳዊ ነገር ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ እያደረጉ ነው ስትል ቤጂንግ ትወነጅላለች፡፡

ይህ እርምጃ የቻይና መንግስት ጎጂ የሆኑ አመለካከቶች በበይነመረብ ሚዲያዎች እንዳይሰራጩ በማድረግ የማህበረሰቡን ማህበራዊ እሴቶች ለመጠበቅ ያቀደው ትልም አካል ስለመሆኑ ነው የተነገረው፡፡ አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv