InternationalNews

የአረብ ኤምሬትስ ጥቃት

🔸አረብ ኤምሬትስ በኒውክለር የኃይል ማመንጫዋ ላይ ጥቃት እንደተፈፀመባት አስታወቀች።

🔸አረብ ኤምሬትስ እንዳለችው ትላንት እሁድ ነው በብቸኛው የኒውክለር ጣቢያዋ ላይ ነው ጥቃት የተፈፀመው።

🔸የኤምሬትስ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳለው ከምዕራቡ የአገሪቱ ድንበር ሦስት ድሮኖች ጥሰው ከገቡ በኋላ ነው ጥቃቱ የደረሰው።

🔸በዚሁ ጊዜ ሁለት ድሮኖች ተመተው መውደቃቸውን ሚኒስቴሩ ገልፆ አንደኛው ድሮን ግን የኒውክለር ተቋሙን የኤሌክትሩክ ጀኔሬተር መቶታል።

🔸ጥቃቱ የደረሰው ከኒውክለር ጣቢያው ዋና ጊቢ ውጭ በሚገኝ የኤሌክትሪክ ጄኔሬተር ላይ እንደደረሰ ተጠቁሟል።

🔸የኤምሬትስ ባለስልጣናት በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ያሉ ሲሆን ከኒውክለር ኃይል ማመንጫው ያፈተለከ አደገኛ ጨረር አለመኖሩን እየተናገሩ ነው።

🔸ኤምሬትስ ለጥቃቱ ኢራንን በቀጥታ ከማውገዝ ይልቅ ድርጊቱ የአሸባሪዎች ፀብ አጫሪ ድርጊት ነው ማለትን መርጣለች።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews