InternationalNews

የኢራን ምላሽ

🔸አሜሪካና እስራኤል ኢራንን ደግመው በሚሳኤል ይደበድባሉ መባሉን ተከትሎ ኢራንም በቂ ምላሽ እሰጣለሁ እያለች ነው።

🔸የኢራን መንግስት ቴሌቪዥን በጠላቶቻችን ላይ ተነሱ የሚል ቅስቀሳ ለዜጐቹ እያስተላለፈ ሲሆን በርካታ ኢራናዊያን መሣሪያ ታጥቀው በየቦታው እየታዩ ነው።

🔸ኢራን ትጥቅ ማጠባበቅ የጀመረችው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት በተቀዛቀዘው ድርድር መካከል ኢራን ጊዜ እያለቀባት ነው እርምጃ የምንወስድ ከሆነም በምድሯ ላይ የሚተርፋት ነገር የለም ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያቸው ከፃፉ በኋላ ነው።

🔸በሌላ በኩል ኢራን የጠቀሳቸው የቴህራን ነዋሪዎች የኒውክለርና የሚሳኤል ቴክኖሎጂዎቻችን እንደ ድንበራችን ሁሉ የምንሰዋላቸው ናቸው እያሉ ነው።

🔸ነዋሪዎቹ ትራምፕ ጥቃት የሚሰነዝሩብን የኒውክለር ቦምብ እንደሌለብን እያወቁ ጭምር ነው ሲሉ ተደምጠዋል። በሌላ በኩል የሁለቱ አገራት አደራዳሪ ፓኪስታን ለተጨማሪ ንግግር አደራዳሪዎቿን ወደ ቴህራን ልካለች።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews