የኢትዮጵያና እንግሊዝ አጋርነት
ኢትዮጵያና እንግሊዝ በአጠቃላይ ልማትና በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር መስማማታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል።
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ እና የዓለም ባንክ ዓመታዊ የፀደይ ወቅት ስብሰባ በዋሺንግተን ዲሲ ለቀናት እየተካሄደ ቆይቷል።
ከዚህ ስብሰባ ጎን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ከእንግሊዙ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ጋር የሃገራቱን አጋርነት ከማስፋት ባለፈ በንግድ ፣ በልማትና በኢንቨስትመንት እንዲሁም በኢኮኖሚ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል ተብሏል።
የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ሚኒስትር ባሮኒስ ቻፕማን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ዙሪያ ያላትን ሚና አንስተው የእንግሊዝ መንግስት የልማት አጋርነቱን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
