EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ትንበያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በመጪው ዓመት 10.2 በመቶ እድገት ሊያመዘግብ ይችላል ተብሎ መተንበዩን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት የበጀት ዓመቱን ሶስተኛ የ100 ቀናት የሥራ አፈፃፀም እና የዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም በገመገሙበት ጊዜ ላይ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ9.2 በመቶ እያደገ ይገኛል ብለዋል።

የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት በፈረንጆቹ 2026 አመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ9.2 በመቶ ሊያድግ ይችላል ሲል መተንበዩ ይታወሳል።

መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይፋዊው የማህበራዊ ገፅ የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv