InternationalNews

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሀገራቸው አሜሪካና ኢራን በደረሱበት የመግባቢያ ስምምነት እንደማትገዛ ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ማሳወቃቸው ተሰምቷል።

ሲ ኤን ኤን ቴሌቪዥን ጣቢያ የእስራኤልን ባለስልጣናት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ከቀጣዩ የአሜሪካና ኢራን ድርድር የመጨረሻ ውጤት ይመጣል ብለው እንደማይጠብቁ ጠቅሷል፡፡

ኔታንያሁ ኢራን በኒውክሌር ፕሮግራሟ ዙሪያም ሊቀመጡ የሚችሉ ክልከላዎችን በቁምነገር ትቀበላለች ብለው እንደማያምኑ የተነገረ ሲሆን በዚህም ምክንያት እስራኤል ለዚህ የመግባቢያ ስምምነት ተገዥ አትሆንም ተብሏል፡፡

የእስራኤሉ መሪ ይህንን የሀገራቸውን አቋም ለፕሬዝዳንት ትራምፕ ግልጽ ማድረጋቸውና እራሷን ችላም በሄዝቦላና ሌሎች የቀጠናው ታጣቂዎች ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራ እንደምትቀጥል መናገራቸውም ነው የተገለጸው፡፡

እስራኤል በሊባኖስ ላይ እየፈጸመች ያለችው ጥቃት አሁንም መቀጠሉ ሲነገር ትላንትና በፈጸመችው ጥቃትም ከ18 በላይ ሰዎች መገደላቸውና በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews