EthiopiaNews

የውጭ ሀገር ዜጎችን በማገት 15 ሚሊየን ብር የጠየቁ 3 ፓኪስታናውያን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተገልጿል።

የፓኪስታን ዜግነት ያላቸው ዝሻን ካሊድ፣ ፍርዝ መሃመድ እና መሀመድ ጀናይድ የተባሉ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሰኔ 4 እና ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጎሮ አትሌቶች መንደር ነው ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ በተከራዩት የመኖሪያ ቤት ውስጥ የህንድና የባንግላዴሽ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች በመያዣነት በመጠቀም የግል ተበዳዮችን በገመድ በማሰርና በፕላስተር በማፈን ከ15 እስከ 30 ሚሊየን ብር በመጠየቅ ጥቃት አድርሰውባቸዋል ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ።

ተጠርጣሪዎቹ በተጨማሪም  ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የገቡ 4 የህንድ ዜጎችን በማሰርና በመደብደብ ከ15 እስከ 25 ሺህ የህንድ ሩፒ አስልኩ በማለት ጥቃት ሲፈጽሙባቸው እንደነበር የግል ተበዳዮች ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባከናወነው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ለወንጀል ድርጊት ሲጠቀሙበት ከነበረው ቢላዋ፣ ገመድና ፕላስተር እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘቦች ጋር በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv