የዕርዳታ ስራዎች መስተጓጎል
በመካከለኛው ምስራቅ በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በዓለም አቀፍ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ላይ የደረሰው መስተጓጎል በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሕፃናት የሚቀርቡ ሕይወት አድን ቁሳቁሶችን አደጋ ላይ መጣሉን ዩኒሴፍ አስታውቋል።
ከውጭ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ የሕፃናት ክትባቶች የአየር ትራንስፖርት ማጓጓዣ ዋጋ ከ50 እስከ 70 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን የጠቀሰው ድርጅቱ በተጨማሪም ለሀገሪቱ ዋነኛ የሰብአዊ ረድኤት መግቢያ በር የሆነው የጅቡቲ ኮሪደር በወደቦች መጨናነቅ ምክንያት በዕርዳታ አቅርቦት ላይ መዘግየትን እየፈጠረ ይገኛል ነው ያለው።
ይህንን ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ቀውስ ለመቋቋምም ድርጅቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሕፃናት አልሚ ምግቦችን የሚያመርቱ የአገር ውስጥ አምራቾችን አቅም በማጠናከር ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
