የፋይናንስ ድጋፍ ለቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ
ባንክ ኦፍ ቻይና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በፋይናንስ ለመደገፍ ጠንካራ ፍላጎት እንዳለው መግለፁ ተነገረ።
የገንዘብ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑክ በአዲሱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ የፋይናንስ ድጋፍ ዙሪያ ከቻይና ባንክ ጋር መነጋገሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ልዑኩ በውይይቱ ስለ ፕሮጀክቱ ቴክኒካዊ ንድፍ፣ የአፈጻጸም ጊዜ እና አጠቃላይ የፋይናንስ መዋቅር ማብራሪያ መስጠቱ ተገልጿል።
ባንኩ በበኩሉ በፕሮጀክቱ ላይ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት በመግለጽ፤ የፋይናንስ መዋቅሩን ለመረዳት ከፕሮጀክቱ አስተባባሪ የአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ግንኙነት መፍጠሩን አረጋግጧል።
ባንኩ በአፍሪካ የሚካሄዱ ፕሮጀክቶችን ቅድሚያ በመስጠት እንደሚደግፍ እና ለቢሾፍቱ አየር ማረፊያ የፋይናንስ ድጋፍ ለማቅረብ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።
መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
