EthiopiaNews

የ2.3 ትሪሊየን ብር በጀት

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ከ2 ትሪሊዮን 339 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሆን ወስኖ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መርቷል።

ለመደበኛ፣ ለካፒታል፣ ለክልሎች ድጋፍና ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ የሚውለው የ2019 አ.ም በጀት ከ2 ትሪሊዮን 339 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሆን መወሰኑን ነው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያስታወቀው።

ምክር ቤቱ በጀቱ የአሥር ዓመቱን መሪ የልማት ዕቅድና የማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፍን መነሻ በማድረግ የተዘጋጀ እንደሆነ ገልጿል።

ምክር ቤቱ የፌዴራል መንግስት የ2019 አ.ም ረቂቅ በጀት በማፅደቅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መምራቱን አሳውቋል።

ምክር ቤቱ የመካከለኛው ዘመን (2019 – 2023 ) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊሲካል ማእቀፍ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምፅ ወስኗል። መረጃው ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተገኘ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews