የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መረጃዎች
እስካሁን ባለው የምርጫ ሂደት 50 ሺ 188 የምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተወርቅ ሀይሉ የምርጫ ሂደቱን አስመልክቶ የመጀመሪያውን የዕለቱን መግለጫ በሰጡበት ጊዜ 695 ምርጫ ጣቢያዎች በሰዓቱ አለመከፈታቸውን ነው የገለፁት።
143 የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ በፀጥታ ችግር ምክንያት እንዳልተከፈቱ ሰብሳቢዋ ገልጸዋል፡፡
ይህም በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በሚገኙ አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች በምርጫ ወቅት ባጋጠመ የፀጥታ ችግር ምክንያት መከሰቱና በዚህም የምርጫ ሂደቱ መቋረጡን ነው ያመለከቱት።
ሰብሳቢዋ አክለውም በተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች 39 ሺ 732 ታዛቢዎች መገኘታቸውን አሳውቀዋል።
#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
