የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የምርጫ ታዛቢ ቡድን በተለያዩ የሀገሪቱ የምርጫ ክልሎች ተሰማርቶ የምርጫ ሂደቱን በመታዘብ ላይ መሆኑን አሳውቋል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በአርባምንጭ ከተማ ድምፅ መስጠታቸውን እና የምርጫ ሂደቱን ጭምር መታዘባቸውን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ምክትል ኮሚሽነር ሚዛኔ አባተ የተመራ የኮሚሽኑ የታዛቢዎች ቡድን ደግሞ በባህርዳር ከተማ የተለያዩ ምርጫ ክልሎች ተዘዋውሮ ጉብኝት ማካሄዱ ነው የተገለጸው።
የባህርዳር ከተማ ምርጫ ክልሎችን የታዘበው ቡድኑ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንም አሳውቋል
ቡድኑ በቀጣይ ወደ ጎንደር ከተማ አቅንቶ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እንደሚታዘብም የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ ጠቁመዋል።
#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
