የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ መሪ የሆኑት እዮብ መሳፍንት በአዲስ አበባ ቂርቆስ ወረዳ 9 ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጽ ሰጥተዋል።
ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክትም እስካሁን በመላ ሀገሪቱ ባለው የምርጫ ሂደት ችግር እንዳላጋጠመ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።
የእስካሁኑ የምርጫ ሂደት መልካም መኾኑን የገለጹት መሪው የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ማዕከላዊ የፓርቲ ቢሮ አዘጋጅተናል ብለዋል።
አክለውም ካርድ ይዞ ድምጽ አለመስጠት ትክክል አለመሆኑን ጠቅሰው ሁሉም ዜጋ ካርዱን በአግባቡ እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።
#EBS #EBSTVNEWS #ELECTION_2018 #_7696_WN https://t.me/ebstvnews www.ebstv.tv
