የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ይሄን ያሉት ዛሬ የኮሚሽኑን የ 2018 በጀት አፈፃፀም አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
ኮሚሽነሩ በበጀት ዓመቱ 725.25 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 738.144 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ነው የገለጹት።
የገቢ አሰባሰቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ322.4 ቢሊዮን ብር ወይም 77.56 በመቶ ብልጫ ማሳየቱንም ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።
መረጃው ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘ ነው።
