የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) ይሄን ያሉት ዛሬ የኮሚሽኑን የ 2018 በጀት አፈፃፀም አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
በአጠቃላይ 28.9 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች እንዲሁም የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 1 ሺህ 835 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ተናግረዋል።
ኮሚሽነሩ በአጠቃላይ በኮንትሮባንድ እና ንግድ ማጭበርበር ሀገር ልታጣ የነበረውን 380.1 ቢሊዮን ብር ማዳን ተችሏልም ብለዋል።
መረጃው ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የተገኘ ነው።
