ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የበረራ ስልጠና እና ምርምር ማእከል ለማቋቋም የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር መፈራረሙን አስታወቀ።
የቦይንግ የአፍሪካ ቀጠና ኃላፊ ሄኖክ ተፈራ ቦይንግ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በደረሰው ዘላቂ የትብብር ስምምነት መሰረት የበረራ ስልጠና ማእከሉ በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ውስጥ እንደሚቋቋም ተናግረዋል።
ኃላፊው ማእከሉ ልዩ የምርምር ፣ ስልጠና እና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚሰጥ እና ለበረራ ተማሪዎች እና ስራ ፈጣሪዎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
ሄኖክ ተፈራ የአፍሪካ አየር መንገዶች በቀጣይ 20 አመታት ውስጥ 1ሺ 2 መቶ አውሮፕላኖች እና ከ74 ሺ በላይ የበረራ ባለሙያዎች እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ከቦይንግ ጋር የተፈረመው ስምምነት ታሪካዊ መሆኑን ገልፀው የበረራ ማእከሉ ምስረታ እንዲሳካ እንሰራለን ብለዋል።
ቦይንግ ኩባንያ በኢትዮጵያ ባለፉት 5 በሰጣቸው ልዩ ልዩ የበረራ ስልጠናዎች ከ14 ሺ በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉ መረጃዎች ያመለክታሉ። መረጃው ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና ከቦይንግ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
