የብሔራዊ ባንክ ይሄን ያስታወቀው ትናንት በገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ የቀረበውን ምክረ ኃሳብ ማፅደቁን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።
ባንኩ ይሄን መመሪያ ያፀደቀው የወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን ለማሻሻል ፣የገበያ ላይ መተማመንን ለመገንባት እና የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማሳለጥ በማለም ነው ብሏል።
የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴው የውጭ ምንዛሪ ኮሚሽን ምጣኔ ከ2.5 በመቶ ወደ 1.5 በመቶ እንዲቀንስ ያቀረበው ምክረ ሃሳብ በብሔራዊ ባንክ ቦርድ መፅደቁን የባንኩ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ ( ዶ/ር ) ተናግረዋል።
ኮሚቴው የውጭ ምንዛሪ ኮሚሽን ምጣኔን እንዲቀንስ የወሰነው ከሸቀጦች ገቢ ንግድ ጋር የተያያዙ ወጭዎችን ለመቀነስ ፣የዋጋ ግሽበት ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ ለመቀነስ እና የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማሳደግ ነው ተብሏል።
ብሔራዊ ባንክ በ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ መጠን መጨመሩን ገልፆ ከሪፎርሙ በፊት ከነበረው በ20 እጥፍ አድጓል ብሏል፡፡ መረጃው ከብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
