የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ትናንት ባካሄደዉ 3ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ የመዲናዋ የ2019 በጀት ዓመት በጀት 502 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር እንዲሆን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡
የፀደቀው በጀት ከባለፈው የ2018 ዓ/ም ተመሳሳይ በጀት ጋር ሲነጻፀር የ152 ነጥብ 26 ቢሊዮን ብር ወይም 43 ነጥብ 5 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስተዳደሩ ገልጿል፡፡
ከፀደቀው በጀት ውስጥ 359 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለካፒታል፣ 142 ነጥብ 97 ቢሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ እንዲሁም 16 ቢሊየን ብር የመጠባበቂያ በጀት መሆኑ ተገልጿል።
በጀቱ የከተማ አስተዳደሩን የ10 እና የ5 ዓመት የልማት ስትራቴጂዎች ግቦችንና እና የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማሳካት ያለመ ፣ የኢኮኖሚ ማረጋጋትና የኑሮ ዉድነትን ለማቃለል የሚውል እና የስራ እድል፣ ፈጠራ፣ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከር ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል።
የከተማ አስተዳደሩ ያፀደቀው በጀት የመሠረተ-ልማት ግንባታና ጥገና በዘላቂነት ማረጋገጥ፣ የተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን ኮሪደር ልማትን ጨምሮ መጠበቅና ለማስቀጠል እንደሚውል ተነግሯል። መረጃው ከከተማ አስተዳደሩ ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
