የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ይሄን ያስታወቀው የ2018 ዓ/ም በጀት አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ነው።
ከቪዛ አገልግሎት ጋር ተያይዞም ተቋሙ በበጀት አመቱ 1,046,286 ቪዛ ለዜጐች እንደተሰጠ አገልግሎቱ ገልጿል።
አገልግሎቱ በበጀት አመቱ በአጠቃላይ ከ42 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።
አገልግሎቱ ለትውልደ ኢትዮጵያውያን 32,952 መታወቂያ እንዲሁም ለ21,163 ዜጎች ደግሞ ጊዜያዊና ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ተሰጥቷል ብሏል።
ተቋሙ በበጀት አመቱ 433 የውጭ ዜጎች እና 4,450 ኢትዮጵያውያን በሐሰተኛ ሰነድ የማጭበርበር ድርጊት ሲፈጽሙ ተይዘው ተጠያቂ እንዲሆኑ የተደረገ መሆኑን ገልፆ በሌላ በኩል 21 ግለሰቦች ደግሞ በህገ-ወጥ ድለላ ተጠያቂ ተደርገዋል ብሏል።
አገልግሎቱ 174 ግለሰቦች ኦንላይን የአስቸኳይ ፓስፖርት በህገ-ወጥ መንገድ ሲሞሉ በመያዛቸዉ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱንና ከዚሁ ጋር በተያያዘ 24 ቤቶች እንዲታሸጉ መደረጉን ገልጿል።መረጃው ከኢሚግሬሽናና ዜግነት አገልግሎት የተገኘ ነው።
