በዓለማችን ላይ 10ኛዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ብራዚል ያልተገቡ የንግድ ተግባራትን ስትፈጽም ቆይታለች ያለችው ዋሽንግተን ለዚህ ተግባሯም ብራዚል 25 በመቶ ታሪፍ እንደምትከፍል ጠቁማለች፡፡
ሆኖም ከብራዚል ወደ አሜሪካ የሚገቡ እንደ ቡና፣ ስጋ፣ የብርቱካን ጭማቂ፣ ዘይት፣ የነዳጅ ምርቶችና የአውሮፕላን መለዋወጫዎች የመሳሰሉ ምርቶች ከዚህ ታሪፍ ነፃ መሆናቸው ነው የተመለከተው፡፡
አሜሪካ ለአንድ ዓመት አደረኩት ባለችው ምርመራ ብራዚል በምርት ላይ የሚያጋጥምን ያልተገባ ተግባር በአግባቡ ያለመቆጣጠር፣ ፍትሀዊ ያልሆነ ታሪፍ መጣልና የመሳሰሉ ሕገወጥ የንግድ ተግባራትን ስትፈጽም መቆየቷን አረጋግጫለሁ ብላለች፡፡
