የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ባወጣው መግለጫ በኢራን ላይ በተፈጸመው ጥቃት ቴህራን በሆርሙዝ ሰርጥ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ጥቃት የምታካሂድባቸውን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ማውደሙን አሳውቋል፡፡
ኢራን በበኩሏ ለዚህ የአሜሪካ ጥቃት በባህሬን፣ ዮርዳኖስና ኩዌት በሚገኙ የዋሽንግተን የጦር ሰፈሮች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰዷን ነው የጠቆመችው፡፡
የኢራን ከፍተኛ ተደራዳሪ የሆኑት ሞሐመድ ባጌር ለሀገራቸው መገናኛ ብዙሀን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ደግሞ ሀገራቸው ጥቅም በማታተርፍበት ስምምነት የመገዛት ግዴታ የለባትም ብለዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት በሰጡት መግለጫ ደግሞ ኢራን በቀጣይ ሳምንት በአስቸኳይ ወደ ድርድር ካልተመለሰች ድልድዮቿና የኢነርጂ መሰረተ ልማቶቿን እንደሚያወድሟቸው ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም፡፡
