EthiopiaNews

በአምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ የተመራ የልዑክ ቡድን ዛሬ ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በክልሉ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎለታል።

አምባሳደሩ የንግድ ዲፕሎማሲን ለማስፋፋት፣ የሰላምና የመረጋጋትን አስፈላጊነት ለማጉላት እና የአሜሪካ የውጭ እርዳታ ሊለካ የሚችል ውጤት እንዲያመጣ ለማረጋገጥ ያለመ ጉዞ ማድረጋቸው ተገልጿል።

አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በጎንደር ከተማ ቆይታቸው ከከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሏል።

አምባሳደሩ ትናንት በመቀሌ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።መረጃው ከአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።