የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምርቶች በሀገራዊ ደህንነት ላይ ከሚያደርሱት ስጋት አንፃር ክልከላ እና ገደብ የተደረገባቸው ምርቶች ለይቶ ማስቀመጡን ገልጿል።
ክልከላ የተደረገባቸው እንደ ሳተላይት ኢንተርኔት ሲስተም ያሉ ምርቶች በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደ ሀገር እንዳይገቡ ፣ ከሀገር እንዳይወጡ ወይም ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ሙሉ በሙሉ የተከለከሉ መሆናቸውን አስተዳደሩ ገልጿል።
ገደብ የተደረገባቸው እንደ ስማርት ኢንተራክቲቭ ያሉ ምርቶች ደግሞ ወደ ሀገር ሊገቡ፣ ሊወጡ ወይም ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት ከአስተዳደሩ የደህንነት ማረጋገጫ ፈቃድ ሲሰጣቸው ብቻ ነው ተብሏል።
ማንኛውም አስመጪ፣ ላኪ ወይም ተጠቃሚ የቴክኖሎጂ ምርቶችን ከማስገባቱ ወይም ከማስወጣቱ በፊት ምርቶቹ በየትኛው ምድብ ውስጥ እንደሚወድቁ የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለበት አስተዳደሩ አሳስቧል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በቀጣይ አዋጁ በእነማን ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን ዝርዝር ማብራሪያ እንደሚሰጥ ጠቁሟል።
ዝርዝር መረጃውን በዚህ ሊንክ ማየት ይችላሉ።https://www.facebook.com/share/18uEGMitRF/
መረጃው ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተገኘ ነው።
