የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲን መሠረት ያደረገ፣ የተናበበ ተቋምና ተቋማዊ አደረጃጀት መፍጠር ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በተካሄደበት ወቅት ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ አንዳንድ የስራ መደቦች በኢኮኖሚው ላይ ጫና እየፈጠሩ የሚመጡ መሆናቸውን አንስተው፤ እያንዳንዱ የሥራ መደብ በዝርዝር ታይቶ ሊስተካከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ይህ የአደረጃጀት ማስተካከል እንቅስቃሴ ከሰራተኛ ቅነሳ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ያሳሰቡት ኮሚሽነሩ አክለውም በአገሪቱ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሥራ መደቦች መፈጠራቸውን ጠቅሰዋል፡፡
