EthiopiaNews

በቡና ማቀነባበር ዘርፍ ታዋቂ የሆነው የቻይናው ሁዪቺዋን ዩንግዩ ኩባንያ በኢትዮጵያ የተቀናጀ የቡና ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል።

ኩባንያው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ እስካሁን በአብዛኛው ያለ እሴት ማሻሻያ ወደ ውጭ የምትልከውን የቡና ምርት በቴክኖሎጂ በመደገፍና ጥራቱን በመጨመር፣ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝና በዓለም ገበያ ይበልጥ ተወዳዳሪ እንድትሆን ትልቅ በር ይከፍታል ተብሏል።

ከ2019 ጀምሮ በቻይና ሄናን ግዛት የኢትዮጵያን ቡና ለቻይና ገበያ ሲያቀርብ የቆየው ይህ ኩባንያ፣ አሁን ላይ በቀጥታ በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ ተሳትፎውን ለማሳደግ መዘጋጀቱን ነው የገለጸው።