EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ሻይ እና ቡና ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሻፊ ኡመር ከኢትዮጵያ 10 ከፍተኛ ቡና ገዢ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ የዛሬ አመት 5ኛ ደረጃ የነበረችው ቻይና በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት 3ኛ ደረጃ መያዟን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው የ2018 በጀት ዓመት ወደ ቻይና ከላከችው 48ሺ የሚጠጋ ቶን ቡና 347 ሚሊየን ዶላር ገቢ ማግኘቷ የባለስልጣኑ መ/ቤት መረጃ ያሳያል።

ምክትል ዳይሬክተሩ ቻይና ለኢትዮጵያ የቡና የወጪ ምርት ንግድ አዲስ ገበያ መሆኗን ገልፀው ከሀገሪቱ የሚቀርበው የቡና ግዢ ጥያቄ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል ብለዋል።

ኃላፊው ሻፊ ኡመር የቻይና ገበያ በደንብ ለመጠቀም ሰፊ የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በ 2018 በጀት ዓመት ወደ ውጭ ሃገራት ከላከችው ቡና 3 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷ ይታወሳል። ዘገባው የዥንዋ ነው።