EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ አስመጪዎች እና ላኪዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥርን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት በኩል እንዲያገኙ ፈቃድ መስጠቱን ገልጿል።

ባንኩ ይሄን ያለው የባንኩን የአገልሎት አሰጣጥ የሚያቀል አዲስ የዲጅታል አገልግሎት ማስተዋወቁን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።

ይህ አገልግሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥሮችን በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን አንድ መስኮት አገልግሎት በኩል ያለምንም ውጣውረድ እንዲሰጥ በማስቻል አስተዳደራዊ ሂደቶችን የሚቀንስ እና ፈጣን የንግድ አሰራርን የሚደግፍ ነው ተብሏል።

አዲሱ አገልግሎት የሚመለከተው ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቁጥርን ለሚያወጡ እና አዲስ ፈቃድ ላገኙ አስመጪዎች እና ላኪዎች ብቻ መሆኑን ባንኩ ገልጿል።

ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሂሳብ ቁጥር ያላቸው የንግድ ተቋማት ለሁሉም የገቢ እና የወጪ ንግድ ግብይቶቻቸው ይጠቀሙበት በነበረው ነባር ቁጥር መጠቀም ይችላሉ ተብሏል። መረጃው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተገኘ ነው።