ዳግም ባገረሸው የኢራን ጦርነት ሁለቱም ሀገራት የሆርሙዝ ሰርጥን ለመቆጣጠር የሚፈጽሙት ጥቃት ተጠናክሮ መቀጠሉ የሚገለጽ ሲሆን የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ በበኩሉ የኢራንን ወታደራዊ አቅም እያንኮታኮተ መሆኑን ነው የሚጠቅሰው፡፡
ሆኖም በርካታ መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ እንደሚገኙት ከሆነ አሜሪካ ትላንትና በኢራን ላይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ድልድዮች፣ ባቡር ጣቢያዎችና አውሮፕላን ማረፊያዎች ኢላማ መደረጋቸው ነው የተሰማው፡፡
የኢራን አብዮታዊ ዘብ እንደሚለው ደግሞ በኦማን የሚገኘውን የአሜሪካን የባህር ኃይል ቅኝት ራዳር ስርዓት እንዲሁም በኩዌትና ባህሬን የሚገኙ ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል፡፡
ዘቡ አክሎም በሶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ የልዩ ዘመቻ ማዘዣ ጣቢያ ላይ ጥቃት ፈጽሜያለሁ ብሏል፡፡
