InternationalNews

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቻይና በአሜሪካ ምርጫ ውስጥ ጣልቃ ገብታለች ሲሉ መወንጀላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ከሁለት ወራት በፊት የተደረሰውን ስምምነት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል ተብሏል።

ትራምፕ በ2020ው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወቅት ቤጂንግ በሚሊዮን የሚቆጠሩ መራጮችን መረጃ ማግኘት መቻሏንና በጆ ባይደን እንዲሸነፉ ማድረጓን በድጋሜ ተናግረዋል፡፡

ትራምፕ ይሄን ክስ ያቀረቡት የአገሪቱ ምክር ቤቶች የሚድ ተርም ምርጫ ሦስት ወራት ሲቀሩት ነው።

ፕሬዝዳንቱ ትላንትና ከዋይት ሀውስ በሰጡት መግለጫ የሀገራቸው የምርጫ ስርዓት አደጋ የተጋረጠበት መሆኑን ጠቁመው ቻይናን ቢወነጅሉም ቤጂንግ ይህንን የትራምፕን ውንጀላ መሰረተ ቢስ ስትል ከማስተባባል ባለፈ በመሰሉ ድርጊት እንደማትሳተፍ ጠቁማለች፡፡

የአሜሪካ የደህንነት ተቋም ከዚህ ቀደም ባወጣው ሪፖርት ቻይና በ2020ው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጣልቃ አለመግባቷን ቢያረጋግጥም ትራምፕ ዳግም ይህንን ውንጀላ ማሰማታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ያሻክረዋል ተብሏል፡፡