EthiopiaNews

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሐምሌ 15 ቀን 2018 አ.ም ጀምሮ አዲሱን የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት ለማግኘት በተቋሙ የበይነ መረብ ቅጽ ላይ መመዝገብ እንደሚችሉ ይፋ አደረገ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ይሄን ያሉት ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ዋና ዳይሬክተሯ አዲሱን የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት አገልግሎት በውጭ አገር በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች በኩል ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

አገልግሎቱ በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ከሐምሌ 15 በኋላ የፓስፖርት ማመልከቻ ምዝገባዎችን በተቋሙ የበይነ መረብ ቅጽ ላይ ብቻ እንዲሞሉ አሳስቧል።