EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ይሄን ያለው በነዳጅ ማደያዎች ላይ አመታዊ የነዳጅ ሜትር ልኬት ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ባስታወቀበት መግለጫ ነው።

ቢሮው በ133 ነዳጅ ማደያዎች ላይ የሜትር ምርመራ ማድረጉን ገልፆ የመቅጃ ኖዝሎች የልኬት ችግር በታየባቸው 91 ነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አስታውቋል፡፡

በዚህ መሰረት 3 ነዳጅ ማደያዎች ከ20 ሊትር ስታንዳርድ ከ1 ሊትር እስከ 1 ሊትር ከ560 ሚሊ ሊትር አጉድለው በመሸጥ ሸማቹን ህብረተሰብ ሲያጭበረብሩ በመገኘታቸው ክስ እንዲመሰረትባቸው ተደርጓል ተብሏል፡፡

በሱፐርቪዥን ጥፋት የተገኘባቸው 3 የነዳጅ ማደያዎች ደግሞ ከ1ወር እስከ 2 ወር ለሚሆን ጊዜ ምንም አይነት የነዳጅ ምርት እንዳይደርሳቸውና ከትስስር እንዲወጡ መደረጉን ቢሮው ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከ20 ሊትር ስታንዳርድ ከ500 ሚሊ ሊትር እስከ 999 ሚሊ ሊትር ድረስ በማጉድል ህብረተሰቡን ሲጎዱ የነበሩ 21 የነዳጅ ማደያዎች ላይ የመጨረሻ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው አሳውቋል፡፡

ከ20 ሊትር ስታንዳርድ ከ200 ሚሊ ሊትር እስከ 499 ሚሊ ሊትር ድረስ በማጉደል 64 የነዳጅ ማደያዎች ላይ የፁሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡መረጃው ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የተገኘ ነው።