EthiopiaNews

የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ይሄን ያለው በኮምቦልቻ ከተማ በተካሄደ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ላይ ነው።

የቢሮው ኃላፊ ኢብራሒም ሙሐመድ (ዶ.ር) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ ሕገ ወጥ ንግድን በመከላከል ገበያውን ለማረጋጋት መሰራቱን ገልፀው በበጀት ዓመቱ ከ126 ሺህ በላይ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ አሥተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል።

ኃላፊው ኢብራሒም ሙሐመድ አሠራርን በማዘመን፤ የገበያ ማዕከላትን በማስፋት፤ ምርትን በማሠራጨት፤ ሕገ ወጥ ንግዶችን በመቆጣጠር እና በሌሎች ዘርፎች በተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር በበጀት ዓመቱ 1 ሺህ 240 ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።መረጃው ከአማራ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የተገኘ ነው።