በፈረንጆቹ 2022 እና 2024 ዓመታት 8 ነጥብ 6 እና 8 ነጥብ 1 በመቶ የነበረው የአለማችን ረሀብተኛ ህዝብ ቁጥር ባለፈው የፈረንጆች 2025 ወደ 7 ነጥብ 8 ከመቶ መውረዱን የተመድ ሪፖርትን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።
መሻሻሉ የታየውም በእስያና በአፍሪካ ባሉ አንዳንድ ሀገራት በታየው ለውጥ ነው የተባለ ሲሆን በአፍሪካ ለውጥ አሳይተዋል የተባሉት ኢትዮጵያ፣ ታንዛንያ፣ ዚምባቡዌ፣ ሴኔጋልና ዛምቢያ ናቸው።
