EthiopiaNews

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 604 ወንዶችና 192 ሴቶች አመት እንዲሁም 38 ጨቅላ ህፃናት ሲሆን ከተመላሾች መካከል 53 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

‎መስከረም 5/ 2018 አ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ88 ሺህ 800 በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

‎ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን ገልጿል። መረጃው ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።