ባንኩ ይሄን ያለው ዛሬ ባካሄደው የግምገማ መድረክ ላይ ነው።
ብድሩ በግጭት አደጋ በተጎዱ አካባቢዎች ለሚገኙ የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርብ መሆኑን ባንኩ ገልጿል።
ለዝቅተኛ ወለድ የብድር አቅርቦቱ የአውሮፓ ኅብረት እና የጀርመን ልማት ባንክ የ31 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አድርገዋል ተብሏል።
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እና የግሪን ኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ዳይሬክተር ተፈራ በፍቃዱ ብድሩ በተመጣጣኝ የወለድ መጠን ስርዓት የሚቀርብ ነው ብለዋል።
አገልግሎቱ በአነስተኛ የወለድ መጠን በተመረጡ አራት ባንኮች እና አንድ የማይክሮ ፋይናንስ በኩል እንደሚቀርብ ኃላፊው አብራርተዋል።
ብድሩ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች የሚቀርብ ሲሆን፤ ዘርፎችም ማኑፋክቸሪንግ፣ አገልግሎት፣ ንግድ ሥራ፣ ኮንስትራክሽን እና የግብርና ማቀነባበርያ ናቸው።
ከአጠቃላይ የብድር አቅርቦቱ በሴቶች እና በወጣቶች ለተቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች ቅድሚያ እንደሚሰጥ የባንኩ መረጃ ያሳያል።መረጃው ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተገኘ ነው።
