የአየር መንገዱ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ይሄን ያሉት ዛሬ የተቋሙን አፈጻጸም በተመለከተ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ዋና ስራ አስፈጻሚው ገቢው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ20 በመቶ ብልጫ እንዳለውና በ2018 በጀት ዓመት ከተያዘው ዕቅድ ጋር ሲነጻጸር ደግሞ የ9 በመቶ ብልጫ አለው ነው ያሉት።
ዋና ስራ አስፈጻሚው በበጀት ዓመቱ አራት አዳዲስ ዓለም አቀፍ የበረራ መዳረሻዎች መከፈታቸውን እንዲሁም አየር መንገዱ 20 ነጥብ 7 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙን ተናግረዋል።
