EthiopiaNews

በአለም አቀፍ ደረጃ በሰዎች የመነገድ ወንጀል እየተበራከተ መምጣቱና የበይነ መረብን በመጠቀም በርካታ ሰዎች ተጠቂ እየሆኑ ነው ተብሏል።

ይህ የተነገረው ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የጸረ በሰው መነገድ ወንጀል ቀን ኢትዮጵያ ትላንት ለ2ተኛ ጊዜ በብሔራዊ ደረጃ ባከበረችበት ወቅት ነው።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታው ቸርነት ሆርዶፋ የሰዎች ንግድን ለመከላከል እንደ ሃገር ሁለተኛ ስትራቴጂካዊ እቅድ እየወጣ መሆኑን ገልጸው የወንጀል ሁኔታው በየጊዜው እያደገ በመምጣቱ ወንጀሉን ለመከላከል አለም አቀፍ ትብብሮች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።

በአሁን ጊዜ  በተለይም በበይነ መረብ የሚደረግ የማጭበርበር ወንጀል መበራከቱ የተነገረ ሲሆን ወጣቶች ከእንዲህ አይነቱ መጭበርበር እራሳቸውን እንዲከላከሉና እንዲያስተውሉ በመድረኩ ላይ ጥሪ ቀርቧል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv