በዛሬው እለት በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላይ እገዛ የሚያደርጉ የፌደራል፣ የክልልና የከተማ መስተዳደር ተወካዮች ምርጫ እንደሚደረግ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
በጉባኤው 250 አባላት ባሉት 16 ስልታዊ ቡድኖች የተደራጁ ተመካካሪዎች ምክክር መካሄድ መቀጠሉን የጠቆመው ኮሚሽኑ በ250 አባላት የተደራጁ 16 ስልታዊ ቡድኖች ከጥቃቅንና ንዑስ ቡድኖች በተገኙና በተጠናቀሩ የአጀንዳ ምክረሃሳቦች ላይ መምከራቸውን ገልጿል፡፡
ትላትናም ስልታዊ ቡድኖቹ የተሰጡ አስተያየቶች ተካተውበት በድጋሚ የተደራጀውን ቃለ ጉባኤ የጋራ በማድረግ በቀጣይ ለሚደረገው እና 500 ተመካካሪዎችን ለያዙ 8 ቡድኖች ምክክር ዝግጅት ሲያደርጉ ውለዋል፡፡
እስካሁን ባለው ሂደትም ከእያንዳንዱ ስልታዊ ቡድን በተመረጡ 25 የአጀንዳ ምክረሃሳብ አጠናካሪዎች የተጠናቀሩ ምክረሃሳቦችን ያዳመጠው 16ቱ ባለ 250 አባላት ስልታዊ ቡድን በጥቃቅንና በንዑስ ቡድኖች ተነስተው በቀረበው ቃለ ጉባኤ ላይ ያልተካተቱ፣ በአግባቡ ያልተብራሩ ያላቸውን ሃሳቦች ማቅረቡም ይታወቃል፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv
