የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት ወይም ኤልኒኖ አስመልክቶ አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በአዲስ አበባ ያካሄደ ሲሆን ስብሰባው በዚሁ አመት ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋምና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ለማጠናከር ያለመ ነው ተብሏል።
ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት የሆነው ኤልኒኖ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ የሚገኝ ክስተት ነውም ተብሏል፡፡
