EthiopiaNews

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ትላንት የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት መድረክ ከተጓዥ ደንበኞች ትኬት ሽያጭ የተሰበሰበ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በእነዚህ ሀገራት ውስጥ እንደሚገኝና ይሄንን ገንዘብ ለማውጣት እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡

አየር መንገዱ ኤርትራ ውስጥ የሚገኝ ከትኬት ሽያጭ የተሰበሰበ ገንዘብ ለማስመለስ በኤርትራ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ እንደነበር የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው ሁለቱ ሃገራት በገቡበት ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳይ ምክንያት ማሳካት አልተቻለም ነው ያሉት።

በተመሳሳይ በሞዛምቢክ እና በሩሲያ ከባድ ፈተና ገጥሞናል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው በሞዛምቢክ በኩል ማስተካከያ በማድረግ የተጠራቀመውን ገንዘብ ለማውጣት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጸው በሩሲያ የሚገኘውንም ገንዘብ አማራጭ መንገድ ፈልገን ለማውጣት እየሞከርን ነው ብለዋል።