አማራ ክልል በ2018 በጀት ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ 357 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መላኩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ያካሄደ ሲሆን የክልሉን የማዕድን ሀብት ከሕገ ወጥ ምዝበራ ለመታደግ በተከናወነ ሥራ ከ133 ሺህ 500 በላይ ሜትር ኪዩብ ሕገ ወጥ ማዕድን መያዙም ተጠቁሟል።
እንዲሁም በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ የቱሪስት የመስህብ ስፍራዎችን በማስተዋወቅ ከጎብኝዎች ከ15 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘት እንደተቻለ የተጠቀሰ ሲሆን በበጀት ዓመቱ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል ነው የተባለው።
