የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአሜሪካው ቦይንግ ኩባንያ የአውሮፕላን አካላትን በጥራት እያመረተ መሆኑ ተነግሯል።
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው ይህን ያሉት ትናንት የአየር መንገዱን የ2018 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።
አየር መንገዱ ለ68 አውሮፕላኖች የሚሆኑ አካላትን በማምረት ለቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ በማቅረብ 6.2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መግኘቱን ገልፀዋል።
ይህንኑ የማምረት አቅም ይበልጥ ለማሳደግ በቂሊንጦ አካባቢ የተገነባው ግዙፍ ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ ምርት እንደሚጀምርም ዋና ስራ አስፈፃሚው አንስተዋል።
